Page Last Updated On: Sat, September 17, 2011
|
 
 
   
የዜናዎቹን አርዕስት እዚህ ይምረጡ

 

ለ418 ባለሀብቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
አልሚ ባልሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ለ328 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ
የ2002 የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ

ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ተጠቆመ

10.6 ቢሊየን ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ መስጠቱ ተገለጸ

በክልሉ በቱሪዝምና ሆቴሎች ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚመጡ ምቹ ሁኔታ እንዳለ ተጠቆመ

 
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ለ305 ባለሀብቶች ፈቃድ መሠጠቱ ተገለጸ

ነሐሴ 2003 ዓ.ም

በ2003 በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ከዘርፉ የክልሉን ህዝብ ዘላቂ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወነ ባለው ተግባር ለ4,822 ቋሚና ለ13,460 ጊዜያዊ ዜጐች የሥራ ዕድል ማስገኘት የሚችሉ ብር 2,540,679,893 ካፒታል ላስመዘገቡ 305 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሠጠቱን የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዩሱፍ ሳኒ ገለጹ፡፡

ከየካቲት 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በታቀደ መልኩ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በጀት ዓመቱንና በክልሉ እየተተገበረ ያለዉን 44,400,924,544 ብር ካፒታል የተመዘገበውን የስኳር ፕሮጀክትን ጨምሮ  ለ1,336,295 ዜጐች ቋሚና ጊዜያዊ ዜጎች የሥራ እድል ማስገኘት የሚችሉ 109,404,028,721.54 ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 5,854 ባለሀብቶች በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ መሠማራት እንዲችሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሠጠቱንና የፕሮጀክቶቹም ስርጭት ከሴክተር አንጻር ሲታዩ 1480 በእርሻ፣397 በአግሮ ኢንዱስትሪ 114 በኮንስትራክሽን 11 በኢነርጂ፣1008 በሆቴልና ቱሪዝም ፣ 1039 በኢንዱስትሪ፣344 በሪልስቴት፣894 በአገልግሎትሰጪ 546 በማህበራዊ አገልግሎት እና 21 በንግድ መሆኑንም አቶ ዩሱፍ ገልጸዋል ፡፡

ኤጀንሲው ፈቃድ መስጠት ብቻ አይደለም ግቡ ያሉት ኃላፊው ባለሀብቶች ፈቃድ አውጥተው ለልማት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አግኝተው ወደ ልማት ገብተው እራሳቸውን ጠቅመው የክልሉንም ሆነ የሀገር አቀፉን ማህበረሠብ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲችሉ ለማብቃት የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ተግባራት እየተፈጸሙ እንዳሉና በበጀት ዓመቱ ብቻ 3,289 ኘሮጀክቶችን በቅርበት በማየት ተገቢውን እገዛ ማድረግ መቻሉን ፣ለ92 ባለሀብቶች ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን የካፒታል ዕቃና መለዋወጫዎችን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት እንዲችሉ ለፌደራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ መፃፉንና ቀድሞ ሳይለካ ለባለሀብቶች ተሠጥቶ የነበረ 35647.04 ሄ/ር መሬት ተለክቶ ኘላንና ካርታ ተሠርቶለት ባለሀብቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘት እንዲችሉ መደረጉንም ጨምረዉ አብራርተዋል፡፡

የተጀመረውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል በበጀት ዓመቱ በገጠር 22,907.76 ሄ/ር መሬት ለግብርና ኢንቨስትመንት መዘጋጀቱን፣ በከተማም ለጨረታ የተዘጋጀ 1,327,472.88 ካ.ሜ በላይ መሬት መዘጋጀቱን፣ ለባዩ ፊውል ልማት 29,013.13 ሄክታር መሬት በገጠር መዘጋጀቱንና በማዕድንም ዘርፉ ለማሠማራት ለሚፈልጉ በክልሉ የሚገኙና በጥናት የተደረሰባቸው ሀብቶች መረጃ ተደራጅቶ አልሚዎችን እየጠበቀ መሆኑን የገለጹት አቶ የሱፍ ተቋሙ ቀድሞ በIPS ካስጠናቸው 300 የኘሮጀክት ኘሮፋይሎች በተጨማሪ በራሡ ባለሙያዎች በመጠቀም ንጽጽራዊ ጠቃሚነታቸውንና ወቅታዊነታቸውን ከግምት ያስገቡ 15 የኘሮጀክት ኘሮፋይሎች ማጥናቱንና ለባለሀብቶች ዝግጅ ማድረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው ከሀገርም ሆነ ከውጭ ሀገር መጥተዉ በክልሉ ኢንቨስትመንት መሰማራት ለሚፈልጉ ልማታዊ ባለሀብቶች ባሉበት ቦታ ሆነው የኢንቨስትመንት አማራጫቸውን አውቀው በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ ወስነው እንዲመጡ ለማስቻል በተለዩ ፖቴንሻሎች ላይ በመመስረት የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችንና ድህረ-ገጾችን በመጠቀም ከፍተኛ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ ከመሆኑም በላይ በፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮችን፣ ቆንስላዎችን በመጠቀም መረጃዎች የማሰራጨት ሥራ እየተሠራ ከመሆኑም በተጨማሪ  የተለያዩ የሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ንግድ ትሪኢቶችንና ባዛሮችንም ጭምር እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማስተዋወቅ ሥራ ተሠርቷል፡፡ እንዲያውም በበጀት ዓመቱ በየካቲት ወር በአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለ15ኛ ጊዜ ባዘጋጀው የንግድ ትሪኢት ላይ በማሳተፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታንድ በማቅረብና የጐብኝዎችን ቀልብ ከመሳቡም ባለፈ ተገቢውን መረጃ ለተገቢው ሰው በማቅረብ ከሌሎች ድርጅቶች የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ የቤስት ስታንድ ዋንጫ ተሸላሚም ለመሆን በቅቷል በማለት አቶ ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡

የክልሉን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም እና አጠቃላይ አፈጻጸም ለከፍተኛ የመንግስት አካላት፣ለባለሀብቶች፣ ለተመራማሪዎችና ለሌሎች የልማት አጋሮች ወቅታዊና ታማኝ የሆነ መረጃ ለማቅረብ እንዲቻል ዘመናዊ የሆነ የዳታ ቤዝ ስርዓት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ተዘጋጅቶ በዚያው መረጃዎች እየተደራጁ ከመሆኑም በተጨማሪ ኤጀንሲዉ በሚሠራበት ህንጻ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ ቋሚ ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት ለጐብኝዎች ክፍት መሆን የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት አቶ ዩሱፍ ተቋሙ እስከአሁን ያከናወናቸውና እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ያስመዘገቡት ውጤት በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግስት ያስቀመጠው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በዘርፉ ለመሳካቱ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው በቀጣይ 4 አመታት ግብርና መር የሆነውን የሀገራችን የልማት ፖሊሲ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገርና መሠረት ለመጣል በክልሉ19 የሪፎርም /የገቢያ/ መዳረሻ ከተሞች 625.1305 ሄ/ር በላይ መሬት መሠረተ ልማት ተሟልቶለት እንዲዘጋጅ ማድረጉን፣ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ወጪና ጊዜ መቀነስ የሚያስችል የኘሮጀክት ኘሮፋይል በበቂ መጠን ማዘጋጀቱንና ሥራውን በባለቤትነት መምራት የሚያችል አደረጃጀት ለመፍጠር የክልሉን ነባራዊ እውነታ መነሻ ያደረገና በጥናት ላይ የተመሠረተ ሠነድ ተዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው መቅረቡን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ በ2004 በጀት ዓመት በተለያየ ዘርፍ መሠማራት የሚችሉ ለ426 ልማታዊ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመሥጠትና ወደ ልማት ለማስገባት ተገቢውን ዝግጅት ማጠናቀቁን፣10,000 ሄክታር በላይ ለገጠር ኢንቨስትመንት የሚውል መሬት ለማዘጋጀት መታቀዱን በተለይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ  አንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ከሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጭ ወደክልሉ ለመሳብ የተለያዩ የማስተዋወቅ ስልቶችን በመጠቀም ከፍተኛ ስራ እንደሚሰራና ሌሎችም ሥራውንና አሠራሩን ስኬታማ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ለመፈጸም መዘጋጀቱን ገልጸው አሁን ባለን 150,285.18 ሄ/ር የገጠርለግብርና ልማት፣132.75 ሄ/ር ለከተማ ኢንቨስትመንት፣ 29,013.13 ሄ/ር ለባዮፊውል ልማት ፣625.1305 ሄ/ር ለኢንዱስትሪ የተከለለ ቦታ መሬት ከመዘጋጀቱም በተጨማሪ በተጠኑና በተለዩ የማዕድን ሀብቶች እና የቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስትመንቶች ለመሠማራት አቅሙና ፍላጎቱ ያላችሁ ባለሀብቶች ወደ ክልላችን ብትመጡ በተለመደው የተቀላጠፈ አገልግሎት አሠጣጣችን ረክታችሁ እንደምትመለሱ በመጠቆም ጥሪያን አስተላልፋለሁ ሲሉ የኤጀንሱው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዩሱፍ ሳኒ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአንፃሩ የክልሉ መንግስት ማድረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጐላችሁ መሬት ተረክባችሁ ወደልማት ገብታችሁ ያቆማችሁና ጨርሶ ወደ ልማት ያልገባችሁ ባለሀብቶች በገባችሁት ውል መሠረት ወደልማት እንድትገቡ በማለት ጥሪአቸውን በማስተላለፍ በቅርብ ቀናት ወደ ልማት መግባት የማይችሉ ከሆነ ህጉ በሚፈቅደው መሠረት ደረጃውን የጠበቀ እርምጃ በመውሰድና መሬቱን በማስመለስ ለአልሚዎች ለማስተላለፍ የሚገደድ መሆኑነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

 

ወደላይ ሂድ  


ለ100 ፕሮጀክቶች ፈቃድ መሰጠቱ ተገለጸ

የካቲት 2003 ዓ.ም

በበጀት አመቱ መጀመሪያ ግማሽ አመት 582,265,701 ካፒታል ላስመዘገቡ 10,181 ዜጎች ጊዜአዊና ቋሚ የሥራ እድል ማስገኘት ለሚችሉ100 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰጥቶአቸው ወደስራ እንዲገቡ መደረጉን የንግድ ኢንዱስትዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ / ቢሮ ኃላፊ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ሳኒ አሳወቁ ፡፡

The Manager አቶ የሱፍ አያይዘዉም በበጀት አመቱ መጀመሪያው መንፈቅ አመት ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች እስከአሁን ያለዉን አፈጻጸም በካፒታል 63,501,236,826 በሚፈጠር የሥራ እድል1,134,909 ሲያደርሰው ፈቃድ የተሰጣቸውን ፕሮጀክቶችን ደግሞ 5,689 እንዲደርስ አድርጎታል፡፡ አጠቃላይ ፈቃድ የተሰጣቻው ፕሮጀክቶች በሴክተር ሲታዩ 1,429 በግብርና፣387 በአግሮኢንድስትሪ፣101 በኮንስትራክሽን፣11 በኢነርጅ፣ 980 በሆቴልናቱሪዝም፣996 በኢንዱስትሪ፣ 339 በሪል እስቴት፣886 አገልግሎት፣ 539 ማህበራዊ አገልግሎት እና 21ንግድ ሲሆኑ ከባለቤት አንጻር ደግሞ 313 የውጭ ዜጎች፣ 185 የውጭና የሀገር ውስጥ በሽርክና 5,180 የሀገር ውስጥ ሲሆኑ 11 ደግሞ የመንግስት መኆናቸውን በመግለጽ  ኤጀንሲው ለባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት ብቻ ሳይወሰን ከሚያለሙ ባለሀብቶች ጎን በመቆም ከቀረጥ ነጻ ማበረታቻ በመፍቀድ፣ የመሬት መጠቀሚያ የግብር እፎይታ በመስጠት፣ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸዉን በመሸለም፣ በማሰልጠን እና ሌሎችንም ድጋፎች በማድረግ ለበለጠ ስኬት መብቃት እንዲችሉ እያደረገ መሆኑን በማብራራት አስፈላጊውን እገዛ ተደርጎላቸው ወደልማት ለመግበት ያልቻሉትንና ልማታዊ ያልሆኑባለሀብቶችን በመለየት ደረጃውን የጠበቀ እርምጃ የመውሰድ ስራ አየተሰራ ይገኛል፡፡ ለልማት የወሰዱትን መሬትም በማስመለስ ለሌሎች አልሚዎች የማስተላለፍ ስራ ተሰርቷል፡፡ በቀጣይም ወልማት በማይገቡት ጥገኛ ባለሀብቶች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ Trainees on training

ንፈቅ አመቱ ኤጀንሲው አሰራሩ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲችል እከታችኛው መዋቅሩ ድረስ ያሉ ባለሙያዎችን አቅም በስልጠና መገንባቱን የገለጹት ኃላፊው በተለይ በመስሪያቤቱ የመረጃ አያያዝ፣ አደረጃጀትና አተነታተን ዙሪያ 50 ለሚኆኑ የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች 8 ቀን በዳታ ቤዝ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡ ስልጠናውም በክልሉ በኢንቨስትመንቱ ዙሪያ ያለዉን የመረጃ ክፍት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፍ ሥራ አስኪያጁ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል፡፡

አቶ የሱፍ ሲያጠቃልሉ በቀጣይ ወደክልሉ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚመጡ ልማታዊ ባለሀብቶች በተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለእርሻ የተዘጋጀ 136,163.71/ር፣ 20 የክልሉ ሪፎርም ከተሞች ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሆን 798/ መሬት መዘጋጀቱን እና በከተሞችም ለተለያዩ ማህበራዊ ልማት ሊዉሉ የሚገባቸዉ ቦታዎች መዘጋጀታቸዉን በመግለጽ ለልማታዊ ባለሀብቶች ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ወደላይ ሂድ  


አልሚ ባልሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ሐምሌ 2002 ዓ.ም

በያዝነው የባጅት ዓመት 474 የገጠርና የከተማ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡  እርምጃ የተወሰደው በክልሉ በተለያዩ የኢኮኖሚ ሴክተሮች የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ለመለየት በክልል ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት፣ በዞኖች ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያዎችና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት ባለሙያዎች በተደረገው ክትትልና ድጋፍ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመስከረም ወር 2002 የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የሴክተር ዕቅድ ባቀደበት ወቅት ከየዞኖችና ከሀዋሣ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መሰረት በማድረግ ነው፡፡

 በዚሁ ስብሰባ ቀጣይ የተጠናከረ ሥራ እንደሚጠይቅ በጋራ ግንዛቤ በመውሰድ የታመነበትና አልሚ ባልሆኑ ባለሀብቶች ላይ በቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዲቻል የጋራ ዕቅድ ወጥቶ ለአፈፃፀም እንዲያመች የአፈፃፀም ሰነድ ተዘጋጅቶ የከተማ አስተዳደሮችና ማዘጋጃ ቤቶች በእርምጃ ወሳጁ ኮሚቴ እንዲካተቱ መደረጉም አስተዋፅኦ እንዳለው የጠቀሱት የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ም/ኃላፊፋ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ናቸው፡፡

  እስከአሁን በገጠር ኢንቨስትመንት ከተሰማሩት ውስጥ 326 ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው 128 ፕሮጀክቶች ውል የተሰረዘባቸው መሆኑና 20 ፕሮጀክቶች ደግሞ መሬት የተቀነሰባቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 


ለ328 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

ሐምሌ 2002 ዓ.ም

በ2002 የበጀት ዓመት ውስጥ በክልሉና በየዞኖቹ የኢንቨስትመንት የሥራ ሂደቶች ብር 1‚326‚359‚160 ካፒታል ላስመዘገቡ 328 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ፡፡  ፕሮጀክቶቹ በክፍለ ኢኮኖሚ ሲታዩ በግብርና፣ በአገልግሎትና በኢንዱስትሪ ሴክተሮች ሲሆን ከዕቅድ አንፃር ሲታይ  ክንውኑ ዝቅተኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት ሲሸጋገሩ ለ19‚625 ዜጐች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ይታመናል፡፡

በበጀት ዓመቱ ውስጥ ለ13 ፕሮጀክቶች የማስፋፊያ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ27 ፕሮጀክቶች የተሰጠ ሲሆን፣ ለ363 ፕሮጀክቶች የፈቃድ ዕድሣት ለመስጠት ታቅዶ ለ723 ፕሮጀክቶች የፈቃድ ዕድሳት ተደርጓል፡፡  ይህ የፈቃድ መስጠትና ዕድሣት ተግባር ከዕቅድ በላይ የተከናወነ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለ49 ፕሮጀክቶች የፈቃድ ለውጥ ለመስጠት ታቅዶ ለ78 የፈቃድ ለውጥ ተደርጐላቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ ያለው የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመጠቀም እስካሁን ከ57.9 ቢሊዩን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 5‚560 ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ለ1‚150‚880 ዜጐች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ይታመናል፡፡


የ2002 የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ

ሐምሌ 2002 ዓ.ም

«በልማታዊ ባለሀበቱ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እውን ይሆናል!$ በሚል መሪ ቃል በክልሉ 12 ዞኖች የ2002 ዓ.ም የኢንቨስትመት ፎረም ተካሄደ፡፡  ፎረሞቹ ከተካሄደባቸው ዞኖች በደረሰን መረጃ መሰረት ሀዋሣ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በሲዳማ፣ በጌዴኦ፣ በጉራጌ፣ በስልጤ፣ በሀዲያ፣ በወላይታ፣ በዳውሮ፣ በጋሞጐፋ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በቤንች ማጂና በሸካ የየዞኖቹን አስተዳዳሪዎች ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ ባለድርሻ አካላትና በርካታ ባለሀብቶችን ጨምሮ ከ2464 ታዳሚዎች በፎረሙ መሳተፋቸውን ከየዞኑ የደረሰን ሪፖርት ያሳያል፡፡ ፎረሙ መሰረት ያደረገው በበጀት ዓመቱ በፕሮጀክቶቹ አካባቢ በመስክ በተደረገው ክትትልና ድጋፍ በታዩ ጠንካራና ደካማ ጐኖች ላይ የቀረበውን ሪፖርት ተንተርሶ መሆኑን ከየዞኖቹ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት የደረሰን መረጃ ዋቢ በማድረግ ነው፡፡ እንደዞኖቹ ኢንቨስትመንት አስተባባሪዎች ሪፖርት በፎረሙ ትኩረት ከተሰጣቸው የውይይት ርዕሶች በዋናነት በአስፈፃሚና በባለድርሻ አካላት፣ በባለሀብቶች በሚታዩ ችግሮችና በውይይት ወቅት በባለሀብቶች በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡
    
    በውይይቱ ማጠቃለያም በተነሱ ችግሮች ዙሪያ በአስፈፃሚና በባለድርሻ አካላት በኩል የሚታዩ ክፍተቶችን ፈጥነው በመድረሰ መፍትሔ እንዲሰጡ፣ በባለሀብቱ በኩል ያሉ ችግሮች ባለሀብቱ ድርሻውን እንዲወሰድ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ከየዞኑ አስተዳዳሪዎችና ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊዎች ተሰጥቶ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀረቡ ሃሳቦች ተስማምተው፣ ባለሀብቶቹ የቀድሞ አሰራር ቀይረው የመስኖ ውሃ መጠቀም በሚችሉበት አካባቢ ያሉ ፕሮጀክቶች በዓመት ከ1 ጊዜ በላይ ምርት ማምረት እንዲችሉና የላቀ ዋጋ ባለው ምርት በመሰማራት ውጤት እንዲያስመዘግቡ፣ ይህ ካልሆነ ደካማ እንቅስቃሴ በሚያሳዩ ፕሮጀክቶች ላይ መሬት የሚነጠቅ መሆኑን አመራር አካላት አበክረው አስገንዝበዋል፡፡
    
    በመጨረሻም እንደየዞኑ ተጨባጭ ሁኔታ በክልሉ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የሥራ ሂደት በወጣው የማወዳደሪያ መሥፈርት መሰረት በየሴክተሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አልሚ ባለሀብቶች የዋንጫና የሰርተፊኬት ማበረታቻ ሽልማት መሰጠቱን ከደረሰን ሪፖርት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡


ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ተጠቆመ

ሕዳር 2002 ዓ.ም

በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከመስከረም 22 እስከ 23/2002 ዓ.ም. ድረስ በሀዋሳ ከተማ ን/ኢንዱስትሪ ቢሮ ስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ሴክተር ጉባኤ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታገሰ ጫፎ በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ፈቃድ አውጥተው፣ መሬት ተረክበውና አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጐላቸው በገቡት ውል መሰረት  ማልማት  ሲጠበቅባቸው  ወደ ልማት  ባልገቡ  ባለሀብቶች ላይ ደረጃውን የጠበቀ እርምጃ መውሰድ ጊዜ የማይሠጠው ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

13ቱ ዞኖች፣ 8 ልዩ ወረዳዎች፣ ከአንድ ከተማ አስተዳደርና ከ22 የሪፎርም ከተሞች ለተውጣጡና ከ500 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት ጉባዔ አቶ ታገሰ  ልማታዊ መንግስታችን ለህዝብ ጥቅም እየሠራ እንዳለ ገልጸው በክልሉ አንዳንድ ባለሀብቶች በከተማም ሆነ በገጠር ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃድ አውጥተው፣ መሬት ተረክበውና አስፈላጊውሁሉ እየተደረገላቸው የወሠዱትን መሬት ያለ ልማት ከ4 እስከ 5 ዓመታት አጥረው ከማስቀመጣቸውም በላይ የህዝብና የመንግስት ሀብት የሆነውን መሬት እያስተላለፉ እንደሚስተዋሉ በማንሣት አመራሩ እነዚህ ባለሀብቶች ጥገኛ መሆናቸውን በመገንዘብ የተጠናከረ እርምጃ በመውሠድ መሬቱን በማሥመለስ አልሚ ለሆኑ ባለሀብቶች መተላለፍ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲፈጠር አሳስበዋል፡፡

በክልሉ እስከ አሁን 5339 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዳወጡ መረጃዎች እንደሚጠቀሙ የገለጹት ኃላፊው ባለፈው ዓመት በተደረገው ጥብቅ ክትትል 205 ባለሀብቶች  የቃል ማስጠንቀቂያን ፣የጽሁፍን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃ እንደተወሰደባቸውና እስከአሁን ፈቃዳቸው ሙሉ በሙሉ የተሠረዘባቸው 204 መድረሳቸውን ገልጸው በቀጣይም የክልሉ መንግስት የፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢ በተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ በማገዝ አልሚ ያልሆኑትን ባለሀብቶች ከሚያለሙት ነጥሎ የማውጣትና ደንብና መመሪያን የተከተለ እርምጃ በመውሠድ በየደረጃው ላለው አመራር ቁልፍ ተግባር ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ የሱፍ ሳኒ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ በየዞኖችና ከተሞች አስጠንቶ የለየውና በጋይድ ማኘ የተያዘው መሬት በአግባቡ ጥበቃ እየተደረገለት ባለመሆኑ\ በተለይ እታች ያለው አስፈፃሚ አካልና ህብረተሠቡ ስለኢንቨስትመንት ያለው ግንዛቤ የሚጠበቀው ደረጃ ላይ ባለመድረሱ መሬቱ ለተገቢው ልማት እየዋለ እንዳልሆነ ጠቁመው አመራር አካሉ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራትና ኢንቨስትመንቱ በሀገር ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እያበረከተ ያለውን ጉልህ ድርሻ በመገንዘብየተከለሉ መሬቶች ለተገቢው አገልግሎት መዋል እንዲችል በጥብቅ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አቶ የሱፍ አያይዘው በከተሞች አካባቢ እየተደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተቀናጀ፣ በተደራጀና በተናበበ መልኩ ለማካሄድ ሥራዎች ተለይተው ከሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ጋራ የጋራ ስምምነት መፈረሙን ጠቁመው ይኸው አሠራር እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደሚወርድ ገልጸዋል፡፡ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ የቀጣይ ትኩረት መሆኑን ያብራሩት የሥራ ሂደቱ ባለቤት በክልላችን እስከ አሁን በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የታየው እንቅስቃሴና የተመዘገበው እመርታ የክልሉመንግስት ቁርጠኝነት የተረጋገጠበት መሆኑን የሚጠቁም ስለሆነ አመራር አካሉ የሚጠበቅበትን በማድረግ እየተፈጸመ ላለው ታሪክ ባለቤት መሆን እንዲችል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጉባኤው የ2001 ዓ.ም. አጠቃላይ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይ 2002 የሚተገበሩ ተግባራትና ትኩረት የተሠጣቸው ነጥቦችም የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡


10.6 ቢሊየን ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ መስጠቱ ተገለጸ

ሕዳር 2002 ዓ.ም

በክልሉ በ2002 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ አመት 10,610,938,124 ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 58 ባለሀብቶች በተለያዩ መስክ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ም/ኃላፊና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ የሱፍ ሳኒ አሳወቁ፡፡

  እነዚህ ፐሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው ወደ ማምረትና አገልግሎት ወደ መስጠት ሲሸጋገሩ ለ7,442 ዜጐች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ይገመታል፡፡ ኘሮጀክቶች እስከአሁን በክልሉ ፈቃድ ያወጡትን ባለሀብቶች 5,339፣ የተመዘገበውን ካፒታል ወደ 55,598,104,686 /ሃምሳ አምስት ቢሊየን አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ሚሊየን አንድ መቶ አራት ሺ ስድስት መቶ ሰማኒያ ስድስት / ብር ሲያደርሰው የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ደግሞ 1,132,132 እንዲደርስ ማድረጉን አቶ የሱፍ ገልጸዋል፡፡

ፈቃድ ማውጣትና በወጣው ፈቃድ መሠረት የከተማም ሆነ የገጠር መሬት መረከብ ብቻ በራሱ ግብ ያለመሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው የክልሉ መንግስት ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት በየደረጃው ያለውን ህብረተሰብ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ደንብና መመሪያ አውጥቶ የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በህጋዊነት ሽፋን ህጋዊ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ብለው ወደ ኢንቨስትመንቱ የተደባለቁትን ጥገኛ ባለሀብቶች ከአልሚዎች ለመነጠል በተጠናከረ መልኩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሠው እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ፈቃድ ወስደው፣ መሬት ተረክበው የሚጠበቀው ድጋፍ ሁሉ ተደርጐላቸው ወደ ልማት ለመግባት ፍላጐት ባላሳዩትና ለ50,405 ዜጐች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተጠብቀው በነበሩ፣ ብር 2,789,956,143 ያስመዘገቡ 204 ኘሮጀክቶች ላይ ፈቃዳቸውን የመሰረዝ ሥራ መሠራቱንና በቀጣይም ይኽን ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ፈቃድ ወስደው ለበርካታ አመታት ያለ ልማት ታጥሮ የተቀመጠውን መሬት በማስመለሥ ለአልሚዎች እንደሚሠጥ አብራርተዋል፡፡

 አቶ የሱፍ አያይዘው የክልሉ መንግስት የሠጣቸውን ድጋፍ በተገቢው ተጠቅመው እውነተኛ የልማት አጋር መሆን ለቻሉና ምሳሌ ለመሆን ለበቁ ባለሀብቶች በየአመቱ ግልጽ በሆነ መሥፈርት በመለየት እያበረታታ መሆኑን ጠቁመው በ2000 ዓ.ም. የተለያዩ ሽልማትከተሠጣቸው 420 ባለሀብቶች በተጨማሪ በ2001 መጨረሻ ከየሴክተሩ ለተመረጡ 174 ባለሀብቶች ሽልማት መሰጠቱን አብራርተው እየተሸለሙ ያሉ ባለሀብቶች በከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ስሜት ተጠናክረው ሲቀጥሉ በመታየቱ በቀጣይም በባለሀብቱ እየተስተዋሉ ያሉ ክፍተቶችን በማጥናት ክፍተቶችን የሚሞላ ድጋፍ በማድረግ እድገት ማሥመዝገብ ለቻሉ ሽልማቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

ኢንቨስትመንቱ በዘላቂነት ለማስቀጠል ሥራውን አቀናጅቶና አደራጅቶ ለመምራት የሚያስችል የ10 አመት የልማት ኘሮግራም ተነድፎ በተግባር እየተገለጸ ከመሆኑም በተጨማሪ በ2000 ዓ.ም. በገጠር 529,181.233 ሄ/ር፣ በከተማ 756,6898 ሄክታርና በከተማ ኢንዱስትሪ ዞን ደግሞ 856.3 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ ጋይድማኘና የኘሮጀክት ኘሮፋይሎች ተዘጋጅተውለት ልማታዊ የሆነው ባለሀብት ያለውጣ ውረድ ባቀረበው ኘሮጀክት ንጽጽራዊ ጠቀሜታ መሠረት መሬት አግኝቶ ወደልማት እንዲገባ ተደርጐ የነበረ ሲሆን ተግባሩም በ2001 ዓ.ም. ቀጥሎ 55018.11ሄክታር የገጠር 196.01 ሄክታር የከተማ መሬት ተዘጋጅቶ ሲሰጥ መቆየቱንና እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት አቶ የሱፍ በቀጣይም አልሚ ባለሀብቶች ከመሬት አንፃር ያላቸውን ፍላጐት ለማሟላት ከ307,295.7 ሄክታር በላይ መሬት  መኖሩንና በየደረጃው ካለው ህብረተሠብ ጋር በመመካከር በስፋት ለማዘጋጀት እቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ እየተጀመረ መሆኑን ከሰጡት ማብራሪያ መረዳት ተችሏል፡፡

 መንግስት መሬት የሚያልቅ ሀብት መሆኑን በመገንዘብ ለጥገኞች መጠቀሚያ እንዳይሆን የአስተዳደር ስርዓቱን የለወጠ በመሆኑ ከዚህ በኋላ አልሚ ባልሆኑ ባለሀብቶች እጅ የሚገባበት እድል መዘጋቱን ያስገነዘቡት አቶ የሱፍ የማልማት አቅምና ፍላጐት ያላቸው የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጐች በክልሉ ኢንቨስት ለማድረግ ቢመጡ ከመቼውም በላይ በፍቅር ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊው ሁሉ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ወደላይ ሂድ  


በክልሉ በቱሪዝምና ሆቴሎች ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚመጡ ምቹ ሁኔታ እንዳለ ተጠቆመ

ሕዳር 2002 ዓ.ም

የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት አቶ የሱፍ ሳኒ በቱሪዝምና ሆቴሎች ኢንቨስትመንት መሰማራት ፍላጐት ላላቸው ባለሀብቶች ክልሉ አዋጭ መሆኑን ገለጹ፡፡

እስከ ሩብ አመቱ መጨረሻ 4,336,560,445.52 ካፒታል ያስመዘገቡ ለ44,524 ዜጐች የስራ እድል የሚያስገኙ 929 ኘሮጀክቶች በሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሠማርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ባለሀብቶች መኖራቸውን ያብራሩት አቶ የሱፍ ክልሉ ከ56 በላይ የሚሆኑ የራሣቸው ቋንቋ፣ ባህልና የአኗኗር ስርዓት ያላቸው ብሔር ብሔረሰቦች ተፈቅረውና ተከባብረው የሚኖሩበት፣ በርካታ ታሪካዊ፣ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት በመሆኑና ወደ ክልሉ የሚገቡ የቱሪስት ፍሰት በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ የቱሪስቱን ምቾት የሚጠብቅና የቆይታ ጊዜውን የሚያራዝም አገልግሎት ለመስጠት ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በመገንባት መንቀሳቀስ ለሚፈለጉ ባለሀብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ህዝቦች መካከል መቀራረብንና መግባባትን በመፍጠር በዓለም ሰላምን ከማበርከቱም በተጨማሪ ለሀገር ኢኮኖሚ ያለው ጠቀሜታ የላቀ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው እስከአሁን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች እያበረከቱ ካለው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ቀጣይ በሆቴሎችና ቱሪዝም ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ አልሚ ባለሀብቶች በየከተማው ከ379.72622 ሄ/ር በላይ መሬት በጋይድ ማኘ በማስደገፍ መዘጋጀቱን አብራርተው በዘርፉ መሠማራት ለሚፈልጉ ሁሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ፎረሙ አልሚው ባለሀብትና ከፍተኛ አመራሩ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ስኬት ዙሪያ ያገጠሙ ችግሮች በጋር እውቀት መፍትሄ የሚያገኘበት፤ ጠቃሚ ልምዶች ደግሞ ተቀሞረው የአሰረር ስርዓት የሚሆኑበት መሆኑን የገለፁት አቶ ሽፈራው በሥራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እንዲነሱ አደርገዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችም በቂ ምላሽ ተሠጥቷል፡፡ ለሁለት ቀናት ሲከሄድ የቆየው ፎረምም በክልሉ ኢንቨስትመንት ተሠማርተው ስኬት ላስመዘገቡ 174 ባለሀብቶች እንደየአፈጻጸማቸው የምስክር ወረቀት፣መዳሊያና የዋንጭ ሽልማት እንዲያገኙ ተደርጐ ተጠናቋል፡፡


ልማታዊ ባለሀብቱ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገበው ተገለፀ፡፡
በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ከሰኔ 28-29/2ዐዐ1 ዓ/ም ድረስ የልማታዊ ባለሀብቱን ምረጥ ተሞክሮዎች በማስፋፋት የኢትዮጵያን ህዳሴ በጽኑ መሰረት ላይ እንገነባላን በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ፎረም ላይ በማገኘት ልማታዊ ባላሀብቱ የጀመረውንና ስኬታማ እየሆነ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስገንዝበዋል፡፡

ከ8ዐዐ በላይ የሚሆኑ ልማታዊ ባለሀብቶችና የክልሉና የዞኖች ከፍተኛ አመራሮች በተሳተፉበት ፎረም ላይ አቶ ሽፈራው እንዳብራሩት የክልሉ መንግስት ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የነዋሪውን ህዝብ ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጭ ውጤት ማስመዝቡን ገልጸው የተመዘገበውን እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል በክልሉ በተለያየ ዘርፍ የተሰመራው ባለሀብት የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ለዚሁም የክልሉ መንግስት ከጐናቸው እንደማይለይ አረጋግጠዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የልማት ቀጠናዎችንና ኮሪደሮችን በመለየት፤ በከተማም ሆነ በገጠር ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የሚውል መሬትን በማዘጋጀት፤ አልሚዎች እንዲያውቁት በማድረጉ እስከ አሁን በክልሉ ከ521ዐ በላይ ኘሮጄክት በተለያየ ዘርፍ ፈቃድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ የገለፁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቀጣይም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ዜጐችን እንደየጥያቄያቸው ለመስተናገደ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡


ለ657 ኘሮጀክቶች ፈቃድ መስጠቱ ተገለጸ!!
በክልሉ በሚገኙ 13 ዞኖች፣ 8 ልዩ ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ 4,396,219, 236 /አራት ቢሊየን ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ ሠላሰ ስድስ ብር/ ካፒታል ያስመዘገቡ 117,759 ዜጐች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ 657 ኘሮጀክት በተለያዩ ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባታቸውን የንግድና ኢንዲስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ የሱፍ ሳኒ አሳወቁ፡፡
አቶ የሱፍ አያይዘውም ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ተጠንቶ በሙከራ ትግበራ ውጤታማነቱ የተረጋገጠው መሠረታዊ የአሠራር ለውጥ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ከመደረጉ በተጨማሪ 657 በተለያዩ ክፍለ ኢኮኖሚዎች ለመሰማራት ፍላጐት ያላቸው ኘሮጀክቶች ፈቃድ በማውጣት መሬት ተረክበው ወደ ሥራ የሚገቡበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡በክልሉም የተመዘገበው ካፒታል 43,22,7111,ዐ92 ሲደርስ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል 1,ዐ3ዐዐዐ ሆኗል፡፡ የአጠቃላይ ኘሮጀክቶቹም ቁጥር ደግሞ 521ዐ እንዲደርስ አስችሎታል፡፡ ቀደሞ በሥራ ላይ የነበሩ ኘሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ሥራው ተሠርቷል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ሳይቀሩ ኘሮጀክቶችን እስከሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ አፈጻጸማቸውን በማየት የተሻለ እንቅስቃሴ ያላቸውን ለበለጠ ስኬት እንዲበቁ የማትጋት ሥራ የተሠራ ሲሆን ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሳዩት ደግሞ ችግራቸው ተለይቶ መፍትሄ እንዲያገኙ ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ 1162 ኘሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል ተደርጐላቸዋል፡፡ በቀጣይም ይኸው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ሁኔታ ለማሻሻል በክልሉ 2ዐ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ባለሀብቶች የያዙትና እያለሙ ያሉት መሬት እንዲለኩ ተደርጓል ፡፡ በዚሁ መሰረት 72ዐ62.ዐ9ሄ/ር መሬት ተለክቷል፡፡ በአዲስ መልክ የገጠር 55ዐ18.11 ሄክታር መሬት በከተማ ደግሞ 196ዐ1 ሄ/ር መሬት ተዘጋጀቷል፡፡ ወደኘሮጀክት የሚሄድ 6ዐ.5ዐ ኪሎ ሜትር መንገድም መስራቱን አሥረድተዋል፡፡

ፈቃድ ወስደው መሬት ተረክበው በውላቸው መሰረት ወደልማት መግባት ያልቻሉ 1,912, 783, 616 ካፒታል አስመዝግበው የነበሩ 43157 ዜጐች የሥራ ዕድል ይፈጥሩ የነበሩ 173 ኘሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ፈቃዳቸው ተሠርዞ የያዙት መሬት በህጋዊ መልኩ እንዲመለስ ተደርጎ ለሌሎች አልሚ ባለሀብቶች መስጠቱንና በቀጣይም ይኸው ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ የሱፍ ጨምረው አሳውቀዋል፡፡

አቶ የሱፍ ሲያጠቃልሉ ባለñት ወራት የክልሉን አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፖቴንሻል ከማስተዋወቅ፣ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሀብቶች ለማጠናከር፣ ከህብረተሠቡ ጋር ለመስተሳሰርና ልምዳቸውን ለማሥተላለፍ ሰፊ ሽፋን ያላቸውን ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችና የኘሬስ ሚዲያዎችን በመጠቀም በርካታ የኘሮሞሽን ሥራም ሰርተናል፡፡ ይኽንን ተከትሎ የባለሀብት ፍሰት እያደገ መጥቷል፡፡ በክልሉ በአሁኑ ሰዓት 211 የውጭ ሀገር ባለሀብቶች ተሰማርተው እየሠሩ ሲሆን የሀገር ውስጥና የውጭ በሽርክና የተሰማሩባቸው ደግሞ 144 መድረሳቸውን ጠቁመው በቀጣይም በክልሉ ባለኮኮብ ሆቴል ለሚገነቡ፣ ሆስፒታሎችን፣ ታላላቅ የትምህርት ተቋማትን ታላላቅ ኢንዲስትሪዎችን፣ ሰፋፊ እርሻዎችን እና ሌሎችንም ለማልማት ለሚመጡ አቅምና ፍላጐት ያላቸው ባለሀብቶችን ተቀብለን ለማስተናገድ ከመቸውም በላይ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ወደላይ ሂድ   

 
Copy Right © SNNPRs Investment Expansion Process