|
ማስታወቂያ
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ማንኛውንም አገልግሎት
ለማግኘት ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን በሙሉ፡-
የክልሉ መንግስት በክልሉ እያካሄደ ባለው የኢንቨስትመንት ልማት ሀብታቸውን፣ እውቀታቸውንና
ልምዳቸውን ተጠቅመው ለመንቀሳቀስ የሚፈልጉ ልማታዊ ባለሀብቶችና በዘርፉ ማንኛውንም አገልግሎት
ለማግኘት ለሚፈልጉ ደንበኞች በማሰብ በፊት በክልል ብቻ ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶችንም ማለትም
፡-
1.
በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ
እና በባህሪያቸው ተንቀሳቃሽ የሆኑ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እየተዘዋወሩ የሚሰሩ ሌሎች
ኘሮጀክቶች ማለትም የአስጎብኝነት አገልግሎት፣ የመፀዳጃ ቤት ማጽዳት ሥራ
ፈቃድ መስጠት
2.
የእሸት ቡና መፈልፈያ የግንባታ ካርታ መስጠት
3.
የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ መስጠት እና
4.
በክልሉ በሚገኙ ልዩ ወረዳዎች
ማንኛውንም አገልግሎት በክልል ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ከምንሰጥ በስተቀር ጊዜን፣ ወጪን፣
ፍታሀዊነትንና
ተደራሽነትን ለማጠናከር ሲባል ሌሎች አገልግሎቶች በሙሉ በክልሉ በሚገኙ 14 ዞኖችና ሀዋሳ ከተማ
አስተዳደር እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን አንዳንድ ደንበኞቻችን ከመረጃ እጦት የተነሳ ወደ ክልሉ
በመምጣት ላላስፈላጊ ወጭ እየተዳረጉ መሆኑን ስለገለጹልን ይህን ማስታወቂያ በድህረ-ገፃችን
ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተንዋል፡፡
ስለዚህ ውድ ደንበኞቻችን ድህረ-ገፃችን ላይ በተገለጸው የዞኖቻችን ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
አድራሻ በመታገዝ ከላይ ከጠቀስናቸው አገልግሎቶች በስተቀር ማንኛውንም አገልግሎት በዞናችና ሀዋሳ
ከተማ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት
ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
ሀ ዋ ሣ
|